የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አንቀፅ 366 (1) ፣ 367 (1) እና 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 33 እና 34 መሰረት የግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች 9ኛ መደበኛ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ቁጥር 2 (የቀድሞው ግሎባል ሆቴል) የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስብሰባውን ስለሚያካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔው እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች

  • የአክሲዮን ማህበሩ ስም __________ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
  • የማህበሩ የተፈረመ ካፒታል______123,054,000
  • የማህበሩ የተከፈለ ካፒታል_____ 102,781,000
  • የማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ደ/ዘይት መንገድ ጠመንጃ ያዥ ግሎባል ሆቴል ፊትለፊት ጋራድ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 0114705102

የ9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ
  2. ከ8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኋላ የተደረጉ የማህበሩን አክሲዮን ዝውውሮች ተቀብሎ ማጽደቅ
  3. አ.ኤ.አ የ2025/26 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
  4. እ.ኤ.አ የ2025/26 የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
  5. እ.ኤ.አ የ2025/26 ሂሳብ ዓመት የተገኘ የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈልን በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፤
  6. ለቀጣይ ሦስት አመታት ማለትም እ.ኤ.አ ከ2026/27 እስከ 2028/29 ድረስ የሚያገለግል የውጭ ኦዲተሮች ቅጥር እና የሥራ ዋጋ ላይ ተወያይቶ መወሰን
  7. እ.ኤ.አ የ2025/26 ሂሳብ ዓመት ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈል ዓመታዊ የተጣራ ትርፍ ድርሻ (ጉርሻ) ላይ መወሰን
  8. እ.ኤ.አ የ2026/27 ሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈል ዓመታዊ የሥራ ዋጋ መወሰን
  9. የጉባዔውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፡፡

የ5ኛ አስቸኳይ ጉባዔ አጀንዳዎች

  1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጸደቅ፤
  2. የአክሲዮን ማህበሩን ካፒታል ማሳደግ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
  3. የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል፤
  4. የጉባዔውን ቃለ-ጉባኤ ማጸደቅ

ማሳሰቢያ

  • በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክስዮኖች በንግድ ህጉ አንቀጽ 373 መሰረት በወኪሎቻችሁ አማካኝነት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፣ ጉባኤው ከመካሄዱ ሶስት ቀናት በፊት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ጠመንጃ ያዥ ግሎባል ሆቴል ፊትለፊት ጋራድ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት አክሲዮን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 432-6-5 ቀርባችሁ ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀውን የውክልና ስልጣን መስጫ ፎርም መሙላት ይኖርባችኋል፡፡
  • እንዲሁም በውል እና ማስረጃ የተረጋረጠ በጉባዔ ላይ ለመካፈል እና ድምጽ  ለመስጠት ግልጽ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በእለቱ የውክልናውን ዋና እና ኮፒ ይዞ በመቅረብ በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ይችላል፡፡
  • በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ የፋይዳ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፓርት ዋናውንና ኮፒውን ይዛችሁ እንድትቀረቡ እንዲሁም በውክልና በጉባዔው ላይ የሚገኙ ተወካዮች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ዋና እና ፎቶ ኮፒ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
Scroll to Top